ማዘን እያለብክ ለምን ትስቃለክ
ይሉኛል እንዳልስቅ
እንኳንስ የሚያዩኝ እኔም ያስቀኛል
ለምን እንደምስቅ
……….X2………..
ያለሁበት ዓለም ለቅሶ አይታወቅም
በፈረቃ አልቅሼ በፈረቃ አልስቅም
ኢየሱስ የዘላለም ነዋ
ኢየሱስ ሳቄ ነዋ
የዘላለም ነዋ
……..ዘላለሜ ነዋ
……..X2………
ከመክበርም በላይ ክብር ሳለ ራሱ
ወደ ጥልቁ ውርደት እጅግ ወርዳ ነፍሱ
ሰው ለዙፋን ሲሞት ዙፋን ትቶ የሞተ
የራሱን ማይፈልግ ራሱን የሠጠ
በሞት የማይለይ ሞቶ የሚያሻግር
አምጡ ማይል ወዳጅ እንኩ የሚል ፍቅር
ኢየሱስ የዘላለም ነዋ
ኢየሱስ ሳቄ ነዋ
ኢየሱስ የዘላለም ነዋ
……..ዘላለሜ ነዋ
……….X2……..
የአብን ጥም ቆርጦ እኔን ያስደሰተኝ
ዘላለሜን ባርኮ ተደስት ኑር ያለኝ
ደስተኛ ነኛ ሀዘኔን ወስዶታል
የምድር ዘላለሜን የደስታ አድርጎታል
ደስ ይለኛል በመዳኒቴ
ደስ ይለኛል ባዳነኝ ጌታ
ደስ ይለኛል ሕይወት በሆነኝ
ደስ ይለኛል ባዳነኝ ጌታ
የሰውን ልጅ ወዶ ሊሞት የማይሞተው
የአባቱን ፍቃድ ፍቃዱን በመተው
አምላክ ሆኖ ሳለ ከሰውም ተንቆ
ብቻውን ያላጋዥ ያለረዳት ወድቆ
በሚሞትላቸው እየተገረፈ
ፍቅር ተሸንፎ ፍቅር አሸነፈ
ኢየሱስ የዘላለም ነዋ
ኢየሱስ ፍቅር ነዋ
ኢየሱስ የዘላለም ነዋ
……..ስጦታዬ ነዋ
……….X2……..
Thank you for visiting my YouTube channel please don’t forget to like and subscribe
