ተራራው በአዜብ ሐይሉ – Teraraw by Azeb Hailu
አዝማች
ተራራው ግዙፍ ቢመስል
ለእኔ እንጂ ለአንተ አይደለም
በፊትህ ከባድ የሚሆን
የማትችለው አንድ እንኳን የለም
እግዚአብሔር አንተ ኃያል ነህ
ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው
ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ የቱ ነው
አምላኬ አንተ ኃያል ነህ
ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው
ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ ምንድር ነው
፩) አንድ ነገር ሰማሁ እኔም አመንሁ እርሱን
ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ
ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ
የሚጥል የሚያነሳ የሚገድል የሚያድን
ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ
ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ
አንተ ብርቱ ጌታ ከሆንህ የእኔ አባት
ልረፍብህ እንጂ ልጠጋ በእምነት
አንተ ብርቱ ጌታ ከሆንህ የእኔ አምላክ
ሁሉን ለአንተ ትቼ ዝም ብዬ ላምልክህ
ተራራው ግዙፍ…
፪) የሰው ልጅ ያየለ ቢመስለው በዕውቀቱ
ከፀሐይዋ በታች ነገር ሁሉ ከንቱ
ከፀሐይዋ በታች ነገር ሁሉ ከንቱ
አንተ ግን ጌታ ሆይ ለዘላለም ያው ነህ
ሥራህ ሁሉ ግሩም ድንቅ የሆነልህ
ሥራህ ሁሉ ግሩም ድንቅ የሆነልህ
አንተ ብርቱ ጌታ …
ተራራው ገዝፎ ቢታይ
ለእኔ እንጂ ለአንተ አይደለም
በፊትህ ከባድ የሚሆን
የማትችለው አንድ እንኳን የለም
እግዚአብሔር አንተ ኃያል ነህ
ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው
ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ የቱ ነው
አምላኬ አንተ ኃያል ነህ
ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው
ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ ምንድር ነው
ኤረ ለአምላኬ ይህቺ ምንድር ናት?
በጣም ቀላል ናት በጣም ቀላል በጣም ቀላል
ኤረ ለእግዚአብሔር ይህቺ ምንድር ናት?
በጣም ቀላል ናት በጣም ቀላል በጣም ቀላል
ቀላል ነው (፲፪)
ስለዚህ ዝም ብዬ አመልክሃለሁ
ስለዚህ አምላኬ አከብርሃለሁ
ስለዚህ ጌታዬ አመልክሃለሁ
ስለዚህ ዝም ብዬ አመልክሃለሁ
አመልክሃለሁ (፰)
Key Takeaways
- The article discusses the song ‘ተራራው በአዜብ ሐይሉ – Teraraw by Azeb Hailu’.
- The lyrics express themes of strength, faith, and divine support.
- The song contrasts human limitations with the power of God, offering a message of hope.
- Several links to related songs and performances accompany the lyrics.
Estimated reading time: 2 minutes

