
Addisalem Assefa – አዲስአለም አሰፋ
Addisalem Assefa – አዲስአለም አሰፋ
አዲስአለም አሰፋ
ጆሮዬን ልብሳ
ሐጥያት አላገኘህም ስንፍና አልከሰተህም
ስትገዛ አልደከመህም እርጅና አላወቀህም
(X2)
እኔም አላውቅህም የዘመንህ ቁጥር አይመረመርም (X4)
የለህም እኩያ የለህም አምሳያ ትልቅ ነህ ሃሌሉያ (X2)
ትልቅ ነህ ሃሌሉያ (X4)
የነገስታት ወገብ ትጥቅ የምታስፈታ
ሀያል አምላክ የጌቶች ጌታ (X3)
የፍጥረት መገኛ ህያው መሰረት
አትሰላ በአመታት አትደመር በዘመናት አትሰላ በአመታት
የትኛውም ምሁር ሒሳብ አይሰራህ
የትኛውም ሰዓሊ ብሩሽ አይቀባህ
የቱም አንጥረኛ ቀርጾ አያወጣህ
አሐዱ አትባልም ደረጃም የለህ
ኧረ ‘ኔስ ለክብርህ ኧረ ‘ኔስ ለዝናህ
ሽር ጉድ ልበል ላገልግልህ
ጆሮዬን ልብሳ ልኑርልህ
(X2)
ልኑርልህ (X4)
እስኪ የማን ጀግና ሞትን አሸነፈ
እስኪ የማን ጀግና ጨለማን ገፈፈ
እስኪ የማን ጀግና ሲኦልን ድል ነሳ
እየሱስ ብቻ ነህ የይሁዳ አንበሳ
(X2)
እየሱስ ብቻ ነህ ጀግና እየሱስ ብቻ ነህ
እየሱስ ብቻ ነህ ጀግና ዙፋንህ የፀና
(X2)
ዙፋንህ የፀና ዙፋንህ የፀና
መንግስትህ የፀና መንግስትህ የፀና
ኧረ ‘ኔስ ለክብርህ ኧረ ‘ኔስ ለዝናህ
ሽር ጉድ ልበል ላገልግልህ
ጆሮዬን ልብሳ ልኑርልህ
(X2)
ልኑርልህ (X4)
የለህም እኩያ የለህም አምሳያ ትልቅ ነህ ሃሌሉያ (X2)
ትልቅ ነህ ሃሌሉያ (X8)
(X2)