ይገዛ ጉልበቴ – Yigeza Gulbete
በጌቴሰማኒ ለከፋው ስቃይህ
ለአባትህ ፈቃድ ታዘህ እንደጨረስህ
ልቤ ይሩጥልህ ይገዛ ጉልበቴ
በውድ ዋጋ ላንተ ተሽጧል ህይወቴ
ኦሆ ይገባሀል ስለኔ ሞተሃል
ኦሆ ይገባሀል ስለኔ ታመሃል
የጓጓሁለት ከፈቃድህ ካወጣኝ ከለየኝ
ጤና አይሆነኝም አያረካኝ ባዶነቴን አይሞላኝ
የተመኘሁት ይቅርብኝ (3) ኢአየሱሴ አንተ ቅርልኝ (3)
የጓጓሁለት ያምልጠኝ (3) ኢየሱሴ አንተ ትረፈኝ(2) ትረፍልኝ
ኢየሱስ መድሀኒቴ
ኢየሱስ ህይወቴ
ኢየሱስ ዘላለሜ
ኢየሱስ እምነቴ
ከጊዜአዊው ደስታ መነቀፍን መርጦ
ከግብፅ ገንዘብ ይልቅ አንተን አስበልጦ
ሙሴ በፈርኦን ስም እንዳይጠራ
በእምነት እምቢ አለ ፀና ካንተ ጋራ
ኦሆ ትበልጣለህ አንተ እኮ ህይወት ነህ
ኦሆ ትልቃለህ በምን ትተካለህ
